አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ካቀረቡ ከአርባ ቀን በኋላ እና በመጀመሪያ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለብዙ ቀናት ቀጥሎም ምክር ቤቱ ከአንድ ሳምንት በላይ የፈጀ ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ ዶ/ር አቢይ አህመድን የግንባሩ ሊ/ቀመንበር አድርጎ መርጧል። የዶ/ር አቢይ የኢህአዴግ ሊ/መንበር ሆኖ መመረጥ የሚቀጥለዉ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ማን ሊሆን ይችላል በሚል በአትኩሮት ሲጠበቅ ለነበረው ጥያቄ የመጀመሪያ ዙር ምላሽ ሰጥቷል። ለመሆኑ የዶ/ር አብይ መመረጥ የተለመደው የወያኔ የሴራ አካሄድ ውጤት ነዉ? ወይስ ኢህአዴግ የህዝብን እውነተኛ የለውጥ ፍላጎት ሰምቶ መንገዱን ለማስተካከል የወሰደዉ ዕርምጃ ነዉ? የኢህአዴግ ዉሳኔ እነዚህን ጥያቄዎች ያጠቃለለ ጥልቅ ውይይት ተካሂዶበት የተወሰነ መሆኑንና ያለመሆኑን በቅርቡ የምንሰማውና በተግባርም የምናየው ይሆናል።
የዶ/ር አብይ መመረጥ ኢህአዴግ ውስጥ ያሉት እስካሁን የህወሀት ሎሌ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ድርጅቶችና በህወሓት ውስጥም ያሉ